1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጀርመን አዲስ ጥ/መንግሥት የመመስረቱ ጉዳይ 

ማክሰኞ፣ ኅዳር 12 2010

በጀርመን አዲስ የጥምር መንግሥት ለመመስረት የተካሄደው ድርድር ከሽፏል። መ/መንግሥት አንጌላ ሜርክል በሚመሩት የክርስትያን ዴሞክራቶቹ ህብረትና በክርስትያን ሶሻል ህብረት፣ በነፃ ዴሞክራቶችና በአረንጓዴዎቹ ፓርቲዎች መካከል ባለፉት ስምንት ሳምንታት የተደረገው ድርድር ላልተሳካበት ብዙዎች ለዘብተኛውን የነፃ ዴሞክራቶች ፓርቲ ተጠያቂ አድርገዋል።

https://p.dw.com/p/2o00N
Deutschland Merkel und Steinmeier Debatte zum Asylpaket II
ምስል picture-alliance/dpa/W. Kumm

«በሕዝብ የተመረጡት ፓርቲዎች ሕዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል።»

ከጥምሩ መንግሥት ምስረታ ድርድር መክሸፍ በኋላ አዲስ ምርጫ የማድረግ ወይም የውሁዳን መንግሥት ይቋቋም የሚሉት ሀሳቦች እየተሰሙ ነው። የውሁዳኑ መንግሥት ሀሳብ ግን በብዙዎች ዘንድ፣ በመራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ጭምር ድጋፍ አላገኘም።  የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየርም አዲስ ምርጫ ለማስወገድ በማሰብ ሰሞኑን ሲደራደሩ የከረሙትን ፓርቲዎች፣ ላላግባቡዋቸው ጥያቄዎች አስማሚ ምላሾች በማፈላለግ የጥምሩን መንግሥት ለማቋቋም  እንደገና ጥረት እንዲያደርጉ ለማግባባት በዛሬው ዕለት የፓርቲዎቹን መሪዎች በተናጠል ማነጋገር ጀምረዋል።  

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

አርያም ተክሌ