ደቡብ ሱዳን እና የኢጋድ ስብሰባ
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 9 2010ማስታወቂያ
በተቀናቃኞቹ ወገኖች መካከል በጎርጎሪዮሳዊው 2015 ዓም ተደርሶ የነበረው የሰላም ስምምነት ባለፈው ዓመት ከከሸፈ ወዲህ የሀገሪቱ ህዝብ ስቃይና መከራ እየባሰ ሄዷል። ለዚህም የፖለቲካ መሪዎች ተጠያቂዎች ናቸው በማለት በስብሰባው ንግግር ያሰሙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወቅሰዋል። የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ፣ በምህጻሩ ኢጋድ በጠራው በዚሁ ጉባዔ ላይ የአፍሪቃ ህብረት አባል መንግሥታት፣ የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ እንዲሁም፣ ከሁሉም የኑሮ ዘርፎች የተውጣጡ ደቡብ ሱዳናውያን ተሳታፊዎች ሆነዋል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ