1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገር ቤት ገብቷል

ሰኞ፣ መስከረም 1 2010

ከአዲስ አበባ ቀይ ባህርን ተሻግረን ወደ የመን እናቀናለን፡፡ የመን በጦርነት፣ በሽታ እና ረሃብ አበሳዋን እያየች ነው፡፡ በቀድሞ መንግስት ደጋፊዎች እና በአማጽያን መካከል አላባራ ያለው ጦርነት በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መፈናፈኛ አሳጥቷቸዋል፡፡ በዚህ አይነት አጣብቂኝ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውየን አዲስ አመትን እንዴት ተቀበሉት?

https://p.dw.com/p/2jkFi
11.08.2013 DW online Karte Jemen, Saana, Balhaf eng

አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገር ቤት ገብቷል

የመን በጦርነት ላይ ነች፡፡ የሳዑዲ አረቢያ መራሹ ጦር በየጊዜው የአየር ድብደባ ይፈጽመባታል፡፡ በሀገሪቱ የተዛመተው ወረርሽኝ ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ለህመም መዳረጉ ተዘግቧል፡፡ እንዲህ አይነት ችግሮች በተደራረቡባት የመን ኢትዮጵያውያን የአዲስ ዓመት በዓልን እንዴት እያከበሩ ነው? ጥያቄው የቀረበለት የሰንአውን ወኪላችንን ግሩም ተክለ ሃይማኖት “ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው በዓሉን ቢያከብሩም አከባበሩ ከበፊቱ በጣም ቀዝቅዟል” ይላል፡፡ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ወደ ሀገር መግባቱን የሚናገረው ግሩም በኢኮኖሚ ችግርም፣ በስራ ማጣትም “ቀዝቀዝ ብሎ ወዙ መፍዘዙ አልቀረም” ሲል በየመን ያለውን ሁኔታ ያስረዳል፡፡   

 

ግሩም ተክለ ሃይማኖት 

ተስፋለም ወልደየስ

ኂሩት መለሰ