በኦሮሚያ የተካሄደው የስራ ማቆም አድማ
እሑድ፣ ነሐሴ 28 2009ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንትም ከ2007 ዓም ወዲህ ተቃውሞ ባስተናገደው የኦሮሚያ ክልል ውስጥ፣ በብዙ አካባቢዎች ከነሀሴ 17 እስከ 21፣ 2009 ዓም በክልሉ የስራ ማቆም አድማ ተጠርቶ ነበር። ማንነታቸው ይፋ ያልተደረገ ከሀገር ውጭ እና ቄሮ በሚል መጠሪያ በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ኃይላት በማኅበራዊ ደረ ገጾች የጠሩት የዚሁ የስራ ማቆሙ አድማ አስተባባሪዎች እንዳሉት፣ ለአምስት ቀናት ተጠርቶ የነበረው ይኸው የስራ ማቆም አድማ ያስቀመጣቸውን ዓላማዎች በማሳካቱ በሶስተኛው ቀን ፣ ነሀሴ 19፣ 2009 ዓም ተቋርጧል። በአድማው ሰበብ በብዙ የክልሉ አካባቢዎች የንግዱ እና የመጓጓዣው አገልግሎት ተቋርጦ ነበር፣ መንገዶች ተዘግተው እና ስራ ማቆም ባልፈለጉ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች አሽከርካሪዎች ላይም ጥቃት መጣሉ ተሰምቷል። በጅማ በአንድ የገበያ ቦታ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች በጣሉት የእጅ ቦምብ ቢያንስ 13 ሰዎች ቆስለዋል። የስራ ማቆሙ አድማ፣ ምክንያቱ እና ዓላማው የዛሬው ውይይት ርዕስ ነው።
አርያም ተክሌ
ልደት አበበ