1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የተደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነሳ 

ማክሰኞ፣ ግንቦት 28 2010

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለማንሳት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ አጽድቋል።  

https://p.dw.com/p/2yzPA
Äthiopien - Parlament
ምስል DW/Y. Gebregziabher

« በጠ/ሚዉ ግፊትና የሰላም ትጋት አዋጁ ተነስቶአል» የሕዝብ አስተያየት

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደዉ ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለማንሳት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበውን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ አጽድቋል።  አዋጁ እንዲነሳ መንግሥት ያቀረበዉን ረቂቅ ደንብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ከስምንት ተአቅቦ በስተቀር በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል። አዋጁ የፀናበት ጊዜ ሊያበቃ ሁለት ወር ይቀረዉ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈዉ የካቲት ያወጀዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከዉስም፤ከዉጪም ከፍተኛ ተቃዉሞ እና ትችት ገጥሞት ነበር።ታዛቢዎች እንደሚሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ እስካሁን ከወሰዷቸዉ የለዉጥ እርምጃዎች ሁሉ የአስቸኳያ አዋጁ መነሳት ከፍተኛዉ ነዉ። ዉሳኔዉን የተከታተለዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቶአል።

 
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ


አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ