1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የቀጠለዉ ተቃዉሞ

ዓርብ፣ መስከረም 27 2009

በመንግስት በኩል በክልሉ እየተካሄደ ስላለዉ ጉዳይ መረጃ ለመዉሰድ ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም። ይሁን እንጅ የመንግስት መገናኛ ብዙኃኖች በሰበታ ብቻ «ከ40 ሺህ በላይ ሰራተኞችን የሚያሳትፉ 11 ፋብሪካዎችና 60 የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች» መዉደማቸዉን ዘግበዋል።

https://p.dw.com/p/2R1Ap
Äthiopien Unruhen
ምስል Getty Images/AFP/Z. Abubeker

MMT_Protest in Oromia - MP3-Stereo

በዚህ ተቃዉሞ ብዙ የመንግስት ተቋማትና መንግስት ጋር ቁርኝነት አላቸዉ የተባሉ የአንዳንድ ግለሰቦች ንብረት በእሳት መጋየታቸዉም እየተዘገበ ይገኛል። በክልሉ በአንዳንድ አከባብዎች ያሉ ሰዎችን በአከባቢያችሁ ስላለዉ ተቃዉሞዉን እና እየተወሰደ ስላለዉ ርምጃ ያያችሁትን ወይም የሰማችሁትን እንድያጋሩን ጠይቀን ነበር።

የሰበታ ነዋሪ መሆናቸዉን የሚናገሩትና ስማቸዉ  ግን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የጠየቁን ግለሰብ ከተማዋ ከማክሰኞ ከቀትር በኋላ ጀምሮ በፖሊስና በነዋርዎች መካከል ግጭት እንደነበረና ተሸከርካርዎችም መቃጠላቸዉ ተናግረዋል። 

የሻሻማኔ ነዋሪ ነኝ ያሉን በከተማዋ ብዙም አስደሳች ነገር እንደሌለ ይናገራሉ። ህዝቡም ቢሆን የተረጋጋ መንፈስ ላይ አይደለም ብለዋል።
የደቡብ ዋሎ ነዋሪ ነኝ ያሉት ሌላዋ አስተያየት ሰጭ በበኩላቸዉ በኦሮሚያ ክል እየተደረገ ያለዉ እንደምያሳዝናቸዉና  መንግስት እየወሰደ ባለዉ «ዘግናኝ» ርምጃ ደስተኛ እንዳልሆኑም ጠቅሰዋል። 

በመንግስት በኩል በክልሉ እየተካሄደ ስላለዉ ጉዳይ መረጃ ለመዉሰድ ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም። ይሁን እንጅ የመንግስት መገናኛ ብዙኃኖች በሰበታ ብቻ «ከ40 ሺህ በላይ ሰራተኛን የሚያሳትፉ 11 ፋብሪካዎችና 60 የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች» መዉደማቸዉን ዘግበዋል።  

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ