በአፍሪቃ የጸጥታ ጉዳይ የጀርመን ሚና
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 11 2008ማስታወቂያ
ከአፍሪቃ፣ ከአዉሮጳ እና አሜሪካ የተዉጣጡ 60 ከፍተኛ ባለስልጣናት በተሳተፉበት ባለፈዉ ሳምንት አዲስ አበባ ላይ የተካሄደዉ የሙኒክ የጸጥታ ጉባኤ፤ ሽብር እና ጽንፈኝነትን ስለመዋጋት፣ በሰሜን እና ምሥራቅ አፍሪቃ ቀዉስን ስለመከላከልና ማስተዳደርን አስመልክቶ ተነጋግሯል። የአፍሪቃ ሃገራት የዉስጥ ሰላም ወሳኝ መሆኑ ያመለከተዉ ጉባኤ፤ በተለይ በምርጫ ሰሞን በየሃገራቱ የሚታየዉን አመፅና ዉዝግብም በችግርነት ነቅሶ ተወያይቶበታል። በሳምንቱ ማለቂያ ባህር ዳር ላይ በተካሄደዉ የጣና መድረክ ወይም ጣና ፎረም ላይ የተሳተፉት በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ዮአኺም ሽሚት ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት የአፍሪቃ የጸጥታ ችግር፤ የዓለም የጸጥታ ችግር በመሆኑ ጀርመን በምታደርገዉ ድጋፍ ትገፋበታለች። አምባሳደሩን ያነጋገራቸዉ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ