1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር የምትገኘዉ ኢትዮጵያ 

ረቡዕ፣ የካቲት 28 2010

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከፊታችን እሁድ መጋቢት 2 ጀምሮ  ለስብሰባ እንደሚቀመጥ የኢህአዴግ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዉ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማስታወቃቸዉን የሀገር ዉስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

https://p.dw.com/p/2tspI
Flash-Galerie Der Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
ምስል S. Mengist

«መቼ ነዉ ጠ/ሚ የሚሰየመዉ?» የነዋሪዉ ጥያቄ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካፀደቀ በኋላ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሥራ ማቆም አድማዉ መቀጠሉ እየተነገረ ነዉ። ሀገሪቱ እስካሁን ጠቅላይ ሚኒስትር አለመሰየምዋም ሌላዉ መልስ ያላገኘለት ጥያቄ መሆኑ ተመልክቶአል። ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከፀደቀ በኋላ በምን ሁኔታ ላይ ትገኛለች? የአዲስ አበባዉን ወኪላችንን በስልክ አግኝተነዉ ጠይቀነዋል።

  
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
አዜብ ታደሰ