1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በአማራ ክልል የንግድ ተቋማት መዘጋት አድማ

ሰኞ፣ የካቲት 12 2010

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የገበያ ቦታ የንግድ ተቋማት ተዘግተዉ መዋላቸዉን ምንጮች ለዶይቼ ቬለ ገለፁ። በሌላ በኩል ክሳቸዉ የተቋረጠዉ የወልቃይት ማንነት አስተባባሪዎች መካከል ኮነሬል ደመቀ ዘዉዱ ከእስር መዉጣታቸዉ ታዉቋል። 

https://p.dw.com/p/2swdB
Äthiopien 199. Geburtstagsfeier Kaiser Tewodros II.
ምስል Gebeyehu Begashaw

በአማራ ክልል የንግድና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ተቋርጦ ዋለ።

በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ምንጮቻችን እንደጠቀሱት ዛሬ የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርቶች የንግድ ተቋማት ተዘግተዉ ነዉ የዋሉት በወሎ መርሳ የሚገኙ የዶቼ ቬለ ተከታታይ በስልክ እንደገለፁልን ፌደራል ሕዝቡ እንዲወጣ እያስገደደ ነበር።

አድማዉ የተጠራዉ በኢትዮጵያ ዳግመኛ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከመታወጁ በፊት በኦሮምያ ክልል የተካሄደን ተቃዎሞ ተከትሎ በአማራ ክልል የሚታየዉን የድንበር ጥያቄ ፍትኃዊ የሃብት ክፍፍልን በተመለከተ የተጠራ የተቋሞ መረሐ ግብር ነዉ ሲሉ በጎንደር ከተማ ነዋሪ የሆኑ የዶይቸቬለ ተከታታይ ገልፀዉልናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የወልቃይት ማንነት አስተባባሪዎች መካከል ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ እና ሌሎች 10 የፖለቲካ እስረኞች  ዛሬ ከእስር መለቀቃቸዉም ታዉቋል። ዛሬ ከወገራና ከዋልድባ በሽብር ክስ እስር ላይ ከነበሩ 35 ታሳሪዎች መካከል የ 32 መቋረጡን የዶይቼ ቬለ ምንጮች ገልፀዋል። ከነዚህ መካከል መነኮሳት እንደሚገኙበት ነዉ የተነገረዉ።

 

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ