1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በቫይቨርና ዋትስ አፕ ላይ የክፍያ እቅድ

Merga Yonas Bulaዓርብ፣ መጋቢት 30 2008

የኢትዮጵያ ትልቁ የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጭ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ሰሞኑን በቫይበር፣ በዋትስ አፕና መሰል የድምፅ ጥሪ አገልግሎቶች መስጫዎች ላይ ክፍያ ለመጠየቅ እንዳቀደ የኩባንያዉ የሥራ አመራር ለተለያዩ ሚዲያዎች መናገራቸዉ ይታወቃል።

https://p.dw.com/p/1ISEV
Karte Äthiopien englisch

[No title]

በእነዚህ የቴክኖሎጂ ዉጤቶች ላይ ክፍያ ለመጣል የታሰበበት ምክንያት፤ መንግስት ማገኘት የሚችለዉን ከፍተኛ ገቢ ሳያገኝ በመቅረቱና ይህንኑ ቴክኖሎጂ ተጠቅመዉ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን የሚፈፅሙትን ለመቆጣጠር እንደሆነ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ኢትዮ ቴሌኮም ክፍያዉን ለማስፈፀምና እንደተባለዉ ተያየዥ የሕገ-ወጥ ሥራዎችን ለመቆጣጠር «ፖሊሲ ቻርጅ ኤንድ ኮንትሮል ሲስተም» የሚባል አዲስ ቴክኖሎጂ እንደሚጠቀም የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስካያጅ አቶ አንዱአለም አድማሴ መናገራቸዉ ተዘግቧል።

ይህ ቴክኖሎጂ የቫይቤርም ሆነ ዋትስ አፕ አገልግሎት አንድ ሰዉ ሲጠቀም የሚያሰገባዉ ስልክ ቁጥር በኢትዮ ቴሌኮም ኔትዎርክ ተጠቅሞ በመሆኑ፤ በዚህ ዉስጥ ሲያልፍ ክፍያዉን ያስፈፅማል ሲሉ የእንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዉ አቶ ማርቆስ ለማ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። አቶ ማርቆስ ይህ ርምጃ የቴኪኖሎጂዉ ተጠቃሚ ላይ የሚያመጣዉ ተፅእኖ እንዳለም ሳይጠቅሱ አለለፉም።

Symbolbild Whatsapp
ምስል Imago/R. Wölk

ይህ የኢትዮ-ቴሌኮም ርምጃ ሃገሪቱ ዉስጥ በሚካሄዱት ሕዝባዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችም ሆነ የኤኮኖሚ ዉይይቶች ላይ ተጽእኖ ቢኖረዉም በፌስ ቡክ ማህበራዊ ግኑኝነቶችና አገልግሎት ላይ ቀጥተኛ ተፅእኖ እንደሌለዉ ማርቆስ ይናገራሉ።

Screenshot der Internetseite www.viber.com
ምስል viber.com

ይሁን እንጂ ተጠቃሚዎች ይህ ኢትዮ ቴሌኮም ርምጃ አፈና ነዉ ሲሉ አሳባቸዉን የሚገልፁ ጥቂት አይደሉም። አዲስ አበባ ፒያሳ አከባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ ተስፋዬ መርኔ እንዳሉት፤ አንዱ ለግልጋሎት በነፃ የለቀቀዉን፤ ሌላዉ የአገልግሎት ክፍያ መጠየቁን ተችተዋል። ለማፈኛ እንጅ የኢትዮ ቴሌኮም ገቢ የማጣት ሥጋት ምክንያት ሆኖ እንዳልሆነም ይናገራሉ።


ሌላዉ የተክለሃይማኖት አከባቢ ነዋሪ አቶ ካሳሁን በርይሁን በበኩላቸዉ ገና ይሄን ዜና ስሰማ መንግሥት ለማፈኛ ሊመጠቀም እንደሆነ ገብቶኛል ሲሉ ነዉ የገለፁልን። መንግሥት ገቢ አጣሁ ብሎ እነዚህ አገልግሎቶች ላይ ርምጃ ከመዉሰድ በሕገ-ወጥ ስልክ ማስደወል ሥራ ላይ የተሰማሩትን መቆጣጠር አለበት ስሉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ