1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በሳዉዲ የኢትዮጵያዉያን ፍርደኞች እሮሮ

ዓርብ፣ ጥር 11 2010

ጂዛን በሳዑዲ ዓረቢያ ባለዉ እስር ቤት የሚገኙ እና የፍርድ ጊዜያቸውን የጨረሱ ኢትዮጵያውያን ሪያድ ያለው የኢትዮጵያ ኤምባሲም ሆነ ጂዳ የሚገኘው የቆንስላ ጽህፈት ቤት ጉዳያቸውን ተከታትሎ ሊያስፈታቸው እንዳልቻለ ገለጹ፡፡

https://p.dw.com/p/2rAaA
Ethiopian International School Riyadh
ምስል DW/Sileshi Shibru

ከአስር ዓመታት በላይ በእስር የቆዩ ይገኙበታል

በተለያዩ ወንጀሎች ተሳትፈው በመገኘታቸው 15 ዓመት እና ከዚያ በላይ ተፈርዶባቸው የአመክሮ ጊዜያቸውን ጨምሮ ፍርዳቸውን የጨረሱ ከ120 በላይ እንደሚሆኑ የሚናገሩት ኢትዮጵያዊያን መፈታት ከሁለት ዐመት በላይ እላፊ በእስር ቤት መቆየታቸውን በመዘርዘርም ያማርራሉ፡፡

ሪያድ የሚገኘው ዘጋቢያችን ስለሺ ሽብሩ እዚያ ያሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሥራ ኃላፊዎችንም ሆነ የጂዳውን ቆንስላ ኃላፊ ምላሽ እንዲሰጡ ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካለት በዘገባው አመልክቷል፡፡

ስለሺ ሽብሩ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ