የሰርካለም ፋሲል አስተያየት
ሐሙስ፣ የካቲት 1 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መገናና ብዙሀን አቃቤ ህግን ጠቅሰው እንደዘገቡት እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው 746 ታራሚዎች እና ተጠርጣሪዎች ውስጥ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ፓለቲከኛ አንዱአለም ይገኙበታል። አንዱአም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከመንግስት ተቃዋሚ ቡድን ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለዉ እስክንድር የ 18 ዓመት ጽኑ እስራት አንዱዓለም ደግሞ የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸው በእስር ላይ ናቸው። ዶቼቬለ የእስክንድር ነጋን ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲልን በስልክ አነጋግሯል። ቃለ ምልልሱ የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ሰርካለም እስክንድር ከሚለቀቁት መካከል አንዱ በመሆኑ የተሰማትን ለጠየቃት በሰጠችው መልስ ይጀምራል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ