ሶሻል ዲሞክራቶች ለጥምር መንግሥቱ ሊደራደሩ ነው
እሑድ፣ ጥር 13 2010ማስታወቂያ
በጀርመን ምክር ቤት 2ኛ አብላጫ ድምጽ ያለው የሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ (SPD) ለግዙፉ ጥምር መንግሥት ድርድር ፍቃደኝነቱን ዛሬ ገለጠ። በቦን ከተማ ውስጥ የዶይቸ ቬለ የቀጥታ ሥርጭት ከሚተላለፍበት ሕንጻ አጠገብ የተሰበሰቡት የሶሻል ዲሞክራቶቹ 600 የፓርቲው ተወካዮች በጉዳዩ ላይ ድምጽ ሰጥተዋል። በዛሬው ስብሰባ አመሻሹ ላይ 362ቱ የድጋፍ 279ኙ ደግሞ የተቃውሞ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ይልማ ኃይለሚካኤል