ሶማሊያዉያን ስደተኞች እና ዳዳብ
ሰኞ፣ ጥር 16 2008ማስታወቂያ
ካለፈዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2015 ጀምሮ የተመ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን UNHCR በዳዳብ መጠለያ ጣቢያ ከሚገኙ «ፈቃደኛ» የሆኑትን ወደሶማሊያ መመለስ መጀመሩን አስታዉቋል። ድርጅቱ እንደሚለዉ ባለፈዉ ዓመት 6,000 ሶማሊያዉያን ስደተኞችን መልሷል፤ ዘንድሮ ደግሞ 50ሺ ለመመለስ አቅዷል። ሶማሊያዉያኑ ወደሀገራቸዉ መመለሱን ባይጠሉትም በቂ መጠለያ አለማግኘት እና የትምህርት ቤቶች አለመኖር፤ ከፀጥታዉ ስጋት ጋር ተዳምሮ ችግር ፈጥሮባቸዋል። ለአንዳንዶቹ ደግሞ በመጠለያ ጣቢያዉ ያለዉ የፀጥታ ሁኔታ ሀገራቸዉን እንዲመርጡ አስገድዷቸዋል። ስለሁኔታዉ ናይሮቢ የሚገኘዉን ጋዜጠኛ አነጋግረነዋል።
ፋሲል ግርማ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ