1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስደተኞች እና በ«ዩሮታነል» የተፈጠረው ውዝግብ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 23 2007

በሰሜን ፈረንሳይ በካሌ ከተማ የሚገኙ እና ወደ ብሪታንያ ለመግባት የሚፈልጉ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች ሁለቱን ሀገራት በባህር ውስጥ ለውስጥ በባቡር መስመር የሚያገናኘውን «ዩሮታነል» የተባለውን ዋሻ ጥሰው ለመግባት የሚያደርጉት ሙከራ ባለፉት ጥቂት ቀናት ተጠናክሮዋል።

https://p.dw.com/p/1G7XU
Frankreich Flüchtlinge am Eurotunnel Calais
ምስል Reuters/P. Rossignol

በዚሁ ሙከራ ትናንት አንድ የሱዳን ዜጋ የሆነ ስደተኛ የጭነት ተሽከርካሪ ገጭቶት ሕይወቱ አልፋለች፣ አንድ ሌላ ደግሞ ባለፈው የሳምንት መጨረሻ ባደረገው ሙከራ በደረሰበት የመቁሰል አደጋ ዛሬ መሞቱ ተሰምቶዋል። ካለፈው ጥር ወር ወዲህ ከ37,000 የሚበልጡ ስደተኞች «ዩሮታነል»ን ጥሰው ብሪታንያ ለመግባት ሙከራ አድርገዋል። የፈረንሳይን እና የብሪታንያን ባለሥልጣናት ያሳሰበውን ይህንኑ ጉዳይ ተከትሎ፣ የፈረንሳይ የሃገር አስተዳደር ሚንስቴር ትናንት በርካታ ልዩ የፖሊስ ኃይል በካሌ ከተማ አሠማርቶዋል።

ሀይማኖት ጥሩነህ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ