1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስደተኞች የሚሸጡት ለወሲብ ባርነትና ለጉልበት ሥራ ነው

ሰኞ፣ ሚያዝያ 9 2009

ድርጅቱ ከባርነት ያመለጡ ስደተኞችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ መሠረት አንድ ስደተኛ ከ200 እስከ 500 ዶላር ነው የሚሸጠው ። እንደ ድርጅቱ ስደተኞቹ የሚሸጡት ለወሲብ ባርነት እና ለጉልበት ሥራ ነው።

https://p.dw.com/p/2bMOe
Libyen Tripoli Gerettete Migranten
ምስል Getty Images/AFP/Stringer

Beri.Wash.(IOM Report om Migrants traded as slaves ) - MP3-Stereo

ወደ አውሮፓ ለመሻገር፣ ሊቢያ የሚሄዱ አፍሪቃውያን ስደተኞች በሰው አሻጋሪዎች ለባርነት እንደሚሸጡ ዓለም ዓቀፉ የስደት ጉዳይ ድርጅት በምህጻሩ IOM አስታወቀ። ድርጅቱ ከባርነት ያመለጡ ስደተኞችን ዋቢ አድርጎ ባወጣው ዘገባ መሠረት አንድ ስደተኛ ከ200 እስከ 500 ዶላር ነው የሚሸጠው።  በተሸጠበት ስፍራም በአማካይ ከሁለት እስከ ሦስት ወር እንዲቆይ ይደረጋል። ለዚህን መሰል ዘመናዊ ባርነት ከተዳረጉት መካከል የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት ዜጎች እንደሚገኙበት ድርጅቱ አስታውቋል። የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ አለው ። 

 

መክብብ ሸዋ

ኂሩት መለሰ