ስርዓተ ፀሎት ለሚውኒክ የግድያ ሰለባዎች25 ሐምሌ 2008ሰኞ፣ ሐምሌ 25 2008የቀኝ ጽንፈኞችን አስተሳሰብ ያራምድ ነበር የተባለው የ18 ዓመቱ ኢራን ጀርመናዊ ወጣት ከአስር ቀን በፊት በጀርመን፣ የሚውኒክ ከተማ ለገደላቸው ዘጠኝ ሰለባዎች በትናንቱ ዕለት በከተማይቱ ስርዓት ፀሎት ተካሄደ። በዚሁ ስርዓተ ፀሎት ላይ ከሟች ቤተዘመዶች ጎን፣ የጀርመን ፕሬዚደንት ዮአኺም ጋውክ፣ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል፣https://p.dw.com/p/1JZoVምስል picture-alliance/AP Photo/M. Schraderማስታወቂያ[No title]To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio እንዲሁም፣ የከተማይቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የሀይማኖት ተወካዮችም ተገኝተዋል። በስነ ስርዓቱ ንግግር ያሰሙትም ሁሉ፣ የዶይቸ ቬለ የንስ ቲውሮ እንደዘገበው፣ ጀርመን ለወንጀለኞች እና ለሽብር ፈጣሪዎች እንደማትንበረከክ በመግለጽ፣ እሴቶችዋን ጠብቃ እንደምትቆይ አስታውቀዋል። የንስ ቲውሮ/ይልማ ኃይለ ሚካኤል አርያም ተክሌ ነጋሽ መሀመድ