የስዑዲ ነዋሪዎች አስተያየት
ረቡዕ፣ መጋቢት 26 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በበዓለ ሲመታቸው ንግግር ያነሷቸውን ጽንሰ ሐሳቦች ተግባራዊ ለማድረግ በፓርቲያቸው ኢህአዴግ ውስጥ ያለው ስር የሰደደ የጋራ አመራር ይፈቅድላቸዋል ብለው እንደማያምኑ በሪያድ ሳዑዲ ዓረቢያ የሚኖሩ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ በንግግራቸው ትኩረት የሰጧቸውን አበይት ተግባራት ለማከናወን አስተያየት ሰጪዎቹ እንዳሉት በገዢው ፓርቲ ኢህአዲግ እና በመንግስት መካከል ይታያል ያሉትን መርህ አልባ ግንኙነት መልክ ማስያዝ ይገባቸዋል፡፡ ዝርዝሩን ስለሺ ሽብሩ ከሪያድ ልኮልናል።
ስለሺ ሽብሩ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ