ከእስር የተፈቱ ኢትዮጵያውያን ሐገራቸው ተመለሱ
ሰኞ፣ ግንቦት 13 2010ማስታወቂያ
ሳዑዲ አረብያ በምሕረት ከእስር የለቀቀቻቸው ኢትዮጵያውያን እሥረኞች ከትናንት በስተያ አንስቶ ወደ ሀገራቸው ገብተዋል። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር 1085 ከእስር የተለቀቁ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መግባታቸውን ዛሬ በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል። እስረኞቹ የተፈቱት በቅርቡ ሳውዲ አረብያን የጎበኙት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ኢትዮጵያውያኑ እንዲፈቱ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት መሆኑን መንግሥት አስታውቋል። ከሳዑዲ እስር ቤቶች ስለተፈቱ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ የጅዳውን ወኪላችንን ነብዩ ሲራክን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ነብዩ ሲራክ
ኂሩት መለሰ