ተቃዋሚው ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቄ ተከለከልኩ ሲል መንግሥትን ወቀሰ።
እሑድ፣ መስከረም 28 2010ማስታወቂያ
ተቃዋሚው ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቄ ተከለከልኩ ሲል መንግሥትን ወቀሰ። የፓርቲ አመራር አባል የሆኑት አቶ አበበ አካሉ እንዳሉት በአዲስ አበባ ከተማ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሔድ የቀረበው ጥያቄ ከከተማው መሥተዳድር አዎንታዊ ምላሽ ተነፍጎታል። ፓርቲው ፈቃድ ከልክሎኛል ያለውን ሊሞግት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ክስ መመሥረቱንም አቶ አበበ አክለው ገልጠዋል። የአዲስ አበባ መስተዳድር በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም።