እጩ ራይላ ኦዲንጋ ራሳቸውን ከፕሬዚደንታዊው ምርጫ ማግለል
ማክሰኞ፣ መስከረም 30 2010ማስታወቂያ
ኦዲንጋ በሀገሪቱ አስመራጭ ኮሚሽን ላይ እና በምርጫ ሕጉ ላይ ለውጦች እና ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ከመጀመሪያው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ሂደት ወዲህ ያቀረቡዋቸው ጥያቄዎች የሚጠብቁትን መልስ ካላገኙ በድጋሚው ምርጫ እንደማይሳተፉ ያሰሙትን ዛቻ አሁን በዚሁ ውሳኔአቸው እውን አድርገውታል። ይኸው የራይላ ኦዲንጋ ውሳኔ ለመጻዒው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ምን ተፅዕኖ ይኖረዋል? ሸዋዬ ለገሠ ናይሮቢ የሚገኙትን አቶ ፍቅረማርያም መኮንንን በስልክ አነጋግራቸዋለች።
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ