1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሦስቱ የአዉሮጳ መሪዎች ጉባኤ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 17 2008

ለሦስትዮሽ ጉባዔ ትናንት የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልንና የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ፍራንሷ ኦሎንድን ወደ ሃገራቸዉ የጋበዙት ኢጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ማቲዮ ሬንዚ በተለይ ብሪታንያ ከአዉሮጳ ኅብረት አባልነት በሕዝበ ዉሳኔ ከወጣች በኋላ ኅብረቱ በቀጣይ በሚሄድበት አቅጣጫ ላይ ተነጋግረዋል።

https://p.dw.com/p/1Jnh1
Italien Dreiergipfel zwischen Merkel, Holland und Renzi
ምስል Reuters/R. Casilli

[No title]



ትናንት በኢጣልያዋ የቬንቶቴን ደሴት ተሰበሰቡት የሦስቱ ሃገራት መሪዎች በአዉሮጳ ስላለዉ የስደተኞች ቀዉስና፤ በፈረንሳይና ጀርመን ከደረሰዉ የአሸባሪዎች ጥቃት ወዲህ ስላለዉ የድኅነት ጉዳይ ላይ መነጋገራቸዉ ተዘግቦአል። በኤኮኖሚ ጉዳይ ላይም ያተኮረዉ የሦስትዮሹ ስብሰባ በተለይ በከፍተኛ ብድር ዉስጥ የተዘፈቀችዉ ኢጣልያ፤ ከባንክ በተገናኘ ጉዳይ ላይ ላላ ያለ ሁኔታ እንዲገጥማት ከኅብረቱ ይበልጥ ድጋፍ እንድታገኝ ጥረት እንደምታደርግ ተገልጾአል። በጣልያን ሮም የሚገኘዉ ወኪላችን ተክለዝጊ ገ/እግዚአብሄር ዘገባ ልኮልናል።


ተክለዝጊ ገ/እግዚአብሄር


አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ