1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሞያሌን ግድያ በመቃወም ሰልፍ በለንደን ከተማ

ዓርብ፣ መጋቢት 7 2010

ባለፈው ሣምንት ቅዳሜ በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ የመከላከያ ሠራዊት በነዋሪዎች ላይ የፈጸመው ግድያ በየአቅጣጫው ቁጣን ቀስቅሷል። የኮማንድ ፖስቱ ድርጊቱ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት የተከሰተ መሆኑን ቢገልፅም የመከላከያ ኃይሉ ጥቃት ሆን ተብሎ የተፈጸመ የወንጀል ድርጊት እንደኾነ የገለጡ አሉ።

https://p.dw.com/p/2uSvg
Proteste von Äthiopiern in London
ምስል DW/D. Getaneh

Long Q&A London - MP3-Stereo

ባለፈው ሣምንት ቅዳሜ በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ የመከላከያ ሠራዊት በነዋሪዎች ላይ የፈጸመው ግድያ  በየአቅጣጫው ቁጣን ቀስቅሷል። የኮማንድ ፖስቱ ድርጊቱ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት የተከሰተ መሆኑን ቢገልፅም የመከላከያ ኃይሉ ጥቃት ሆን ተብሎ የተፈጸመ የወንጀል ድርጊት እንደኾነ የገለጡ አሉ። የ10 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው፣ ጥቂት በማይባሉት ላይም የአካል ጉዳት ያደረሰው እና በሺህዎች የሚቆጠሩትን ለስደት የዳረገውን የመከላከያ ሠራዊቱን ርምጃ በመቃወም ለንደን ከተማ ውስጥ ዛሬ ሰልፍ ተካሂዷል። የለንደኑን ተቃውሞ ሰልፍ የተከታተለዉን ዘጋቢያችን ድልነሳው ጌታነህን ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ስለሰልፉ በስልክ አነጋግሬው ነበር። ድልነሳው የሰልፉን ዓላማ በማብራራት ይንደረደራል። 

ድልነሳው ጌታነህን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ