1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምሥራቅ አፍሪቃ የሚገኙ አልቢኖዎች ስቃይ

ዓርብ፣ ሰኔ 26 2007

በሰሜናዊ ታንዛንያ ንዴምቤዚ ገጠር ዉስጥ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሞሃመድ ማቡላ ችግረኛ ደሃ ናቸዉ። እንድያም ሆኖ እንደ ታክሲ በሚጠቀሙባት ብስክሌታቸዉ ገንዘብ በማግኘት ቤተሰቡን ለማስተዳደር እየሞከሩ ነዉ። አቶ ሞሃመድ በዚህ ሥራቸዉ የሚያገኙት ገንዘብ እጅግ አነስተኛ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1FrOI
Symbolbild Albinos in Afrika
ምስል Tony Karumba/AFP/Getty Images

[No title]

በዝያ ላይ ከስድስቱ ልጆቻቸዉ መካከል ሁለቱ ፤ ማለት የአራት ዓመት ልጃቸዉ ሲጃና የስድስት ዓመት ልጃቸዉ ዶቶ የቆዳ መንጣት በሽታ አልቢኖ «ሻሾ» ታማሚ በመሆናቸዉ ከፍተኛ ጥበቃን ይሻሉ። ልጆቹ የዚህ በሽታ ተጠቂ በመሆናቸዉ ብቻ በታንዛንያ ኑሮአቸዉ ለአደጋ ተጋርጦአል።

Tansania Albino Mutter und Kind
ምስል picture-alliance/AP Photo/J. Martin

ታንዛንያ ዉስጥ በአብዛኞች የባህል ህክምና አዋቂዎችና የነጋዴዎች ባመጥዋቸዉ አጉል እምነት ምክንያት የአልቢኖዎች ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል። እንደነዚህ ሰዎች እምነት ከአልቢኖዎች አጥንት ልዩ የሆነ የመፈወሻ መድሐኒት ይገኛል። አንድ ምሑራን ገለፃ፤ በታንዛንያ የጥቁር ገባያ ማለትም በዉስጥ አዋቂ በህይወት ይኑርም ይሙትም አንድ አልቢኖ እስከ 65 ሺ ይሮ ይሸጣል። በዚህም ምክንያት ታንዛንያ ዉስጥ አልቢኖዎች ላይ በተደጋጋሚ አደጋ ይደርሳል፤ በድንገት ይገደላሉ፤ ይጠፋሉ፤ በርካቶች አካላቸዉ በአጥቂዎች ተቆራርጦአል። በምዕራባዊ ታንዛንያ ካታቪ መንደር ዉስጥ ባሳለፍነዉ በግንቦት ወር ዉስጥ አንዲት የ 30 ዓመት አልቢኖ አንድ እጅዋ ተቆርጦአል። ይህን ወንጀል ፈፀሙ የተባሉ ስምንት ተጠርጣሪ ተከሳሾች ፍርድ ቀርበዉ መልስ መስጠት ይጠበቅባቸዋል።ንዴምቤዚ ገጠር ነዋሪ የሆነዉ አቶ ሞሃመድ ማቡላ ስለቤተሰቡ ስጋት ላይ ወድቋል። « የምኖረዉ ከጭቃ በተሰራች አንዲት ደሳሳ ጎጆ ዉስጥ በመሆኑ መንግሥት አንድ ለደሕንነታችን ሥጋት ላይ የማይጥል፤ ልጆቼ ያለሥጋት እንቅልፍ ሊተኙበት የሚችሉበት ቤት እንዲገነባልኝ እማጸናለሁ»

ባለፉት ጊዜያቶች አልቢኖዎች ላይ የሚጣለዉ ጥቃት እየበዛ በመምጣቱ፤ የታንዛንያ መንግሥት ምርመራና ክትትል አድርጎ ወደ 200 የሚሆኑ ባሕላዊ ህክምና አዋቂዎች ታስረዋል። በአልቢኖዎች ላይ የሚደርሰዉን ጥቃት ተከትሎ የታንዛንያ ፕሬዚዳንት ጃካያ ኪክዌቴ ባለፈዉ መጋቢት ወር ባደረጉት ንግግር ድርጊቱ « አስቀያሚና የሕብረተሰቡን ስም የሚያጎድፍ» ሲሉ ገልፀዉታል። ታንዛንያ የአልቢኖ ማኅበረሰብ እንደተሰኘዉ ድርጅት ሁሉ በርካታ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በታንዛንያ ለሚገኙትን አልቢኖዎች ከለላ ይሰጣሉ። እነዚህ ድርጅቶች የተለያዩ የማስተማር እና የገለጻ ዘመቻዎችን በማካሄድ የሰዎችን አጉል እምነት በመቀየርና ገንዘብ በማሰባሰብ አልቢኖዎች ደሕንነቱ የተጠበቀ ሕይወትን እንዲያገኙ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸዉ። በአንዳንድ የሃገሪቱ ክፍሎች የታየዉ ጥረትም ዉጤት ማስገኘቱ ተመልክቶአል።

Tansania Albino Kinder
ምስል Getty Images/AFP/T. Karumba

« ቪክቶርያ ሃይቅ አጠገብ ሙዋንዛ በተባለዉ አካባቢ ከጎርጎረሳዉያኑ 2006 ዓ,ም እስከ 2009 ዓ,ም የአልቦኒዎች ደህንነት እጅግ አስከፊ ሁኔታ ላይ ይገኝ ነበር። ከጎርጎረሳዉያኑ 2010 ዓ,ም ጀምሮ ግን አካባቢዉ ላይ በሚኖሩ አልቢኖዎች ላይ የደረሰዉ አንድ ጥቃት ብቻ ነዉ እንደደረሰ ነዉ የተዘገበዉ።»

ይህ ግን ችግሩ ሙሉ በሙሉ ተቀርፉዋል ብሎ የሚደረገዉን ጥረት መተዉ ማለት እንዳልሆነ የፖሊስ ተጠሪዉ ተናግረዋል። አካባቢዉ ላይ አጉል እምነት የተስፋፋ መሆኑም ተመልክቶአል። እንደ ፖሊስ ተጠሪዉ እንደ ቫለንቲኖ ሞሎልዋ መንግሥት አካባቢዉ ላይ በጀመረዉ የትምህር ት መረሃ-ግብር እጅግ አስፈላጊ ነዉ፤ ክፍለ ከተማዉ ላይ የሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች መረሃ-ግብርን ጠቅሰዋል። በተለይ ባዮሎጂ ትምህርትን ለማሻሻል እየታቀደ ነዉ። ተማሪዎች በዚህ የትምህርት ክፍለ ጊዜ አልቢኖ ማለት የቆዳ መንጣት በሽታ ከዘር ወደ ዘር የሚተላለፍ በሽታ እንጂ ከምትሃት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለዉ ይማራሉ።

«የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የምርምር ላብራቶሪ እንዲኖረዉ አዘዋል» «በተሻለ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት እና ስልጠና አጉል እምነትን እየቀነሰ ይመጣል »ማለታቸዉን የፖሊስ አዛዡ ቫለንቲኖ ተናግረዋል።

ምንም እንኳ ብዙ ጥረት ቢደረግም በታንዛንያ የሚገኙ አልቦኖዎች ያለስጋት እንዲኖሩ የሚደረገዉ ጥረት ገና ሙሉ በሙሉ ስኬታማ አይደለም። በርካታ ቤተሰቦች አሁንም የቆዳ ቀለም ችግር ያለባቸዉን ልጆቻቸዉን ይደብቃሉ። ሌሎች ደግሞ ደህንነታቸዉ በሚጠበቅ ማዕከል ልከዉ ትምህርታቸዉን እንዲከታተሉ ያደርጋሉ። በምዕራብ ታንዛንያ ኪጎሚ ገጠር የሚገኘዉ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት «ማዞዚ ካባንጋ» በምሳሌ ይጠቀሳል። ይህ ግን ችግሩ ተቀረፈ ማልት እንዳልሆነ የሶስት አልቢኖ እናት የሆኑት ሃሚዳ ራማዳኒ ይናገራሉ። በኪጎማ ማዕከል አልቢኖዎች በሚጠበቁበትና ትምህርት በሚከታተሉበት ማዕከል ከማኅበረሰቡ ተገልለዉ እንደ እስረኛ ተዘግተዉ እንደተቀመጡ ያህል እንደሚሰማቸዉ ይናገራሉ። «ጥሩ አይሰማኝም ምክንያቱም በተደጋጋሚ ሰዉ መገደሉን እሰማለሁ»

Tansania Albino Frau Mädchen
ምስል picture-alliance/dpa/AP Photo/J. Martin

የ 14 ዓመትዋ ወጣት ዴቦራ ሩገም በእዚሁ የደህንነት መጠበቅያና መማርያ ማዕከል መኖር የጀመረችዉ አንድ የማይታወቅ ሰዉ ሊገላት ከሞከረ ከጎርጎረሳዉያኑ 2010 ዓ,ም በኋላ ነዉ። ዴቦራ በዚህ ማዕከል ጥሩ እንክብካቤን ብታገኝም፤ ቤተሰብዋን እንደምትናፍቅ አልደበቀችም። « ምኞቴ አንድ ጊዜ ቤተሰቦቼን ማየት ነዉ » ስትል ትገልፃለች።

የአንደኛ ደረጃ ትምህርት አስተማሪነት ስልጠናን በከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ያጠናቀቀዉ ቤቶልድ አልፍሪድም አልቢኖ ነዉ። ታንዛንያ ብሩንዲ ድንበር አቅራብያ በሚገኝ ገጠር ነዋሪ የሆኑትን ቤተሰቦቹን ካያቸዉ ብዙ ጊዜያትን አስቆጠረ። እንደ አልፍሪድ ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት ገጠር እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸዉ ቢያዉቅም መሄድ ግን አይችልም። « በተወለድኩበት ገጠር የተማርኩትን ሞያ ማስተላለፍ እችል ነበር» ሲል አልፍሪድ ይናገራል። አልቢኖዎችም ሥራ መስራት ይችላሉ ብሎ ማሳየትና የሰዉን አዕምሮ መቀየር ይፈልጋል። ቢሆንም እሱ ራሱ አልቢኖ በመሆኑ በዚህ ማዕከል ደሕንነቱ እንዲጠበቅ ማድረግ አለበት።

አልቢኖዎች የሚጣልባቸዉን የነቀፊታ አስተሳሰብ ለመቀነስና በማኅበረሰቡ ያላቸዉ ተቀባይነት እንዲጎለብት ፓርላማ ዉስጥ ቢገቡ እጅግ አስፈላጊ ነገርን ሊሰሩ ይችላሉ። በታንዛንያዋ ጎረቤት ሃገር ኬንያ የቆዳ ቀለም ችግር ያለባቸዉ ፓርላማ አባል እንደ ኢሳቅ ሙዋዉራ። ማዉራ በፓርላማ ዉስጥ ስልጣናቸዉ አልቢኖን የሚገድል በእድሜ ይፍታህ እስራት ወህኒ እንዲወርድ የሚያደርግ ሕግ እንዲጸድቅ ሃሳብ አቅርበዋል። « አልቢኒዝም ሶሳይቲ ኦፍ ኬንያ» የተሰኘ በኬንያ የሚኖሩ አልቢኖዎችን የሚረዳ ድርጅትን አቋቁመዉ በዓመት 100 ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ ወደ « 900 ሺ» ይሮ ርዳታ በማሰባሰብ ገንዘቡ ለአልቢኖዎች ርዳታ እንዲዉል አድርገዋል።

08.01.2015 DW Global 3000 Albino Mädchen

ይህ ገንዘብ ለሰዎች መሰረታዊ ፍላጎቶች መርጃ የሚዉል ነዉ። « በገንዘቡ ለአልቢኖዎች የፀሐይ መከለያ ነገሮችን ለመግዛት፤ እንደ ፀሐይ መነፅር እና ኮፍያ ለመግዛት ነዉ።»

እንድያም ሆኖ ስለአልቢኖ ምንነት ትምህርት ገለፃ እንደሚያስፈል ኢሳቅ ሙዋዉራ ያምናሉ። በኬንያ እነዚህ ሰዎች ማጥቃትና መግደል ያልተለመደ ነዉ። እንድያም ሆኖ እነዚህ ሰዎች የተገለሉ ናቸዉ። የማዉራ አባት ልጃቸዉ ማዉራን የሸሹት እንደተወለዱ አልቢኖ መሆናቸዉን ባዩ ጊዜ ነዉ። እንዳየኝ ይላሉ ማዉራ« እኔ የሱ ልጅ መሆኔን ማመን አልፈለገም»

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ