ሜርክል ለአራተኛ ጊዜ መራሒተ መንግሥት ሆነዉ ተመረጡ
ረቡዕ፣ መጋቢት 5 2010ማስታወቂያ
በጀርመን ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያላቸው ሦስት ፓርቲዎች አዲስ ጥምር መንግሥት ለመመስረት የደረሱበትን ስምምነት በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ በፊርማ አጽቀዋል።፡፡ፓርቲዎቹ የተፈራረሙት ሥምምነት በሚቀጥሉት አራት ዓመታት ጀርመንን የሚመራው ጥምር መንግሥት የሚከተላቸውን ፖሊሲዎች የያዘ ነው።
የስምምነቱን መጽደቅ ተከትሎ የሀገሪቱ የተወካዮች ምክር ቤት አንጌላ ሜርክልን መራሂተ መንግሥት አድርጎ ዛሬ ረቡዕ ይሰየማል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ ጀርመናውያን ምርጫ ያካሄዱት ባለፈው መስከረም ወር ሲሆን በምክር ቤት መቀመጫ ያገኙ ፓርቲዎች መንግሥት መመስረት ባለመቻላቸው መራሂተ መንግሥት ሜርክል ሀገሪቱን በሞግዚትነት ሲያስተዳድሩ ቆይተዋል፡፡ መንግሥት ሳይመሰረት የተቆየበት የ171 ቀናት ጊዜ በጀርመን ታሪክ ረጅሙ ነው ተብሎለታል፡፡
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ