1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሙኒክ ጥቃት፥ 10 ሰው ተገደለ

Mantegaftot Sileshiቅዳሜ፣ ሐምሌ 16 2008

በጀርመን ሙኒክ ከተማ የገበያ አዳራሽ 10 ሰው የተገደለበት የትናንቱን ጥቃት ተከትሎ፦ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል ከሀገሪቱ ቁልፍ ሚንስትሮች ጋር ለመምከር የፌዴራል የደኅንነት ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል።

https://p.dw.com/p/1JUQr
Deutschland Tödliche Schießerei in München
ምስል Reuters/M. Dalder

[No title]

በጀርመን የሙኒክ ከተማ የገበያ አዳራሽ ትናንት ጥቃት በማድረስ 9 ሰው የገደለው የ18 ዓመት ጀርመናዊ ኢራናዊ ወጣት ራሱን ማጥፋቱን ፖሊስ አስታወቀ። የ18 ዓመቱ ጥቃት አድራሽ ዴቪድ አሊ ሶንቦሊ ከገበያ አዳራሹ የሚወጡትን ሰዎች በዘፈቀደ እየተኮሰ ሲገድል የሚያሳይ ምስል በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች ተለቀዋል። ፖሊስ የሙኒክ ከተማን ትናት ማምሻውን ሙሉ ለሙሉ ተቆጣጥሮ ቆይቷል። ማንኛውም ሰው እንዳይንቀሳቀስም ታግዶ ነበር። የጀርመን ፖሊስ የትናንቱ ጥቃት የደረሰበትን ምክንያት ለማጣራት ምርመራ እያደረገ ነው።

Deutschland Olympia Einkaufszentrum in München Hauptbahnhof Großeinsatz
ምስል picture-alliance/AP Photo/S. Widmann

ጥቃቱን ያደረሰው የጀርመን እና የኢራን ጣምራ ዜግነት ያለው የ18 ዓመት ወጣት መኾኑን ፖሊስ አስታውቋል። በኦሎምፒያ የገበያ አዳራሽ ከማክዶናልድ ፊት ለፊት በመሸሽ ላይ የነበሩ ዘጠኝ ሰዎችን በዘፈቀደ እየተኮሰ ከገደለ በኋላ ቆየት ብሎ ራሱን ማጥፋቱን ፖሊስ ገልጧል። ከሟቾቹ መካከል ከአንድ የ45 ዓመት ጎልማሳ በስተቀር ሁሉም ከ14 እስከ 20 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች መሆናቸው ይፋ ኾኗል። በትናንቱ ጥቃት 27 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። ሦስቱ አሳሳቢ በሆነ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ተጠርጣሪው ጥቃት አድራሽ ጀርመን ውስጥ በኖረባቸው በርካታ ዓመታት ከዚህ ቀደም አንዳችም የወንጀል ድርጊት ስለመፈጸሙ የሚያሳይ መረጃ እንደሌለ ፖሊስ አስታውቋል። የትናንቱ ጥቃት የሽብር ጥቃት ይሁን አለያም በዘፈቀደ የተደረገ ግድያ ፖሊስ በማጣራት ላይ ይገኛል። መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል የሀገሪቱን የፌዴራል የደኅንነት ካቢኔ ለአስቸኳይ ስብሰባ ጠርተዋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ