1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለዴር ሡልጣን የኢትዮጵያውያን ሠልፍ በእየሩሳሌም

እሑድ፣ ሚያዝያ 7 2010

እየሩሳሌም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች ያስተባበሩት ሠልፍ በጠቅላይ ሚንሥትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ዛሬ ተከናውኗል። ከሦስት መቶ በላይ ሰዎች ሰልፉ ላይ መታደማቸው ተገልጧል።

https://p.dw.com/p/2w5Bq
Demonstration Äthiopier in Jerusalem
ምስል DW/S. Legese

የኢትዮጵያውያን ሠልፍ በእየሩሳሌም

እየሩሳሌም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሃይማኖት አባቶች ያስተባበሩት ሠልፍ በጠቅላይ ሚንሥትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽ/ቤት ፊት ለፊት ዛሬ ተከናውኗል። ከሦስት መቶ በላይ ሰዎች ሰልፉ ላይ መታደማቸው ተገልጧል። በሰልፉ ከተላለፉ ጥሪዎች፦ ዴር ሡልጣን ገዳም ይታደሳል ሲል የእስራኤል መንግሥት የሰጠውን ተስፋ ይጠብቅ፣ ገዳሙን እናድስ፣ እስራኤል የሚኖሩ ቤተ-እሥራኤላውያንም የኢትዮጵያ ቅርስ እንዲጠበቅ ከኢትዮጵያውያን ጎን ኾነው ትብብር ያድርጉ የሚሉት ይገኙበታል።

በዴርሡልጣን ገዳም ይዞታ ላይ ከግብጽ ቤተክርስቲያን ተደጋጋሚ ጫና እንደሚደርስ ይነገራል። ጫናው ከብዙ በጥቂቱ፦ የገዳሙ ይዞታ የእኛ ነው ማለት፣ በዚያም የተነሳ ገዳሙ እንዳይታደስ ማከላከል፣ መነኮሣት አገልግሎት በሚኖራቸው ጊዜ የድምጽ እወካ እና ረብሻ መፍጠር ይገኙበታል።

ዴር ሱልጣን ንጉሥ ሰለሞን ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት ለንግሥተ-ሣባ የሰጣት የኢትዮጵያውያን ቅርስ እንደኾነ ይገለጣል።

ሸዋዬ ለገሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ