1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትሮይካ ማሳሰቢያ

ሰኞ፣ ጥር 28 2010

የቡድኑ አባላት የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ግዴታዎቻቸውን ለመወጣት ወታደራዊ ግጭት እና ጥቃት እንዲያቆሙም ጥሪ አስተላልፈዋል።

https://p.dw.com/p/2sAHf
Südsudan Symbolbild Konflikt
ምስል Getty Images/AFP/C. Atiki Lomodong

ለደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች የተሰጠ ማሳሰቢያ

በደቡብ ሱዳን እና ሱዳን የሰላም ሂደት ንቁ ተሳታፊ የሆነው ትሮይካ የተሰኘው ቡድን አባላት በደቡብ ሱዳን ሱዳን ሰላም እንዲሰፍን አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታወቁ ። የቡድኑ አባላት የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ግዴታዎቻቸውን ለመወጣት ወታደራዊ ግጭት እና ጥቃት እንዲያቆሙም ጥሪ አስተላልፈዋል። ዩናይትድ ስቴትስን ብሪታንያን እና ኖርዌይን ያካተተው የዚህ ቡድን ተወካዮች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ በደቡብ ሱዳን ችግሩ እንዳይባባስ መንግስቶቻቸው የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዳቸውንም ገልጸዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኅይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ,
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 
ኂሩት መለሰ