ለደቡብ ሱዳኑ ረሀብ የአውሮጳ ህብረት እርዳታ
ረቡዕ፣ የካቲት 15 2009ማስታወቂያ
ለጋሾች ለደቡብ ሱዳኑ የረሀብ አደጋ መርጃ የሚውል እርዳታ እየሰጡ እና ቃል እየገቡም ነው ። ከመካከላቸው አንዱ የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ነው ። ኮሚሽኑ ለደቡብ ሱዳኑ ረሀብ መቋቋሚያ የሚውል ተጨማሪ እርዳታ እንደሚሰጥ አስታወቋል ። የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ኮሚሽኑ ለረሀብ አደጋው መርጃ ተጨማሪ 82 ሚሊዮን ዩሮ ይለግሳል ። የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት በምህፃሩ UNICEF እንደሚለው በሱዳኑ ረሀብ ለሞት አደጋ ከተጋለጡት መካከል በርካታ ህጻናት ይገኙበታል ።
ገበያው ንጉሴ
ሂሩት መለሰ