ለዋልድባ መነኮሳት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 18 2010ማስታወቂያ
አቃቤ ሕግ ፖሊስ ምስክሮችን ሊያቀርብ አለመቻሉን እና ያቀረበበትን ምክንያት እንዳልገለፀ በመጥቀስ ያቀረበዉን መከራከርያ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለዉም። በነ አባ ገብረእየሱስ እና አባ ገብረስላሴ ላይ የሚደመጠዉን የአቃቤ ሕግ ምስክርነት ለመታደም በርካታ ሕዝብ ተገኝቶ ነበር። በእለቱ አቃቤ ሕግ የቆጠራቸዉ ምስክሮች እንዳልተገኙ ለዚህም ፖሊስ የሰጠዉ ምክንያት እንደሌለ እና እሳቸዉም እንደማያቁ ለችሎቱ ተናግረዋል። በመሆኑም ለምስክርነት የተቀጠረዉ ለመጀመርያ ጊዜ ስለሆነ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን ብለዋል። በቦታዉ ለተገኘዉ የፖሊስ ተወካይ ችሎቱ ለምን ብሎ ጠይቆ ነበር። እሳቸዉም አላዉቅም ሌላ የሥራ ክፍል ነዉ የሚሰራዉ የሚል ምላሽ መስጠታቸዉ ታዉቋል። የተከሳሶች ጠበቆች በበኩላቸዉ ተከሳሶቹ ባቀረቡት አቤቱታ ምክንያት ወደ ፍርድ ቤት ሲመላለሱ አቃቤ ሕግ በቀጠሮ ሰዓት ምስክሮችን ይዞ መቅረብ እንዳለበት በተደጋጋሚ ማሳሰብያ መሰጠቱን ፤ የምስክርነት ቀጠሮ ለመጀመርያ ጊዜ ነዉ የተሰጠዉ ተብሎ በአቃቤ ሕግ የቀረበ መከራከርያ የሕግም የሥነ ስርዓትም መሰረት የሌለዉ በመሆኑ የሰዉ ምስክር የማሰማት መብቱ ተነፍጎ በሰነድ ማስረጃ ብቻ ብይን ይሰጠን ብለዉ መከራከራቸዉ ታዉቋል።
ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ