ሳዑዲ ዓረቢያ ሴቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ መፍቀዷ ድብልቅልቅ ስሜቶችን ፈጥሯል
ዓርብ፣ መስከረም 26 2010ማስታወቂያ
በሸሪዓ ሕግ በምትገዛው ሳዑዲ ዓረቢያ የአስልምናው ኃይማኖት ዋና ሙፍቲ በጉዳዩላይ አስተያየት ሲሰጡ በድፍኑ "ንጉስ ሰልማን ለሕዝባቸው የሚበጀውን ያውቃሉ" ነበር ያሉት።ይኸ የማሽከርከር ፈቃድ ለአብዛኞቹ የሳዑዲ ሴቶች ፤ በሐገሪቱ ላሉ ባንኮች እና የመኪና አምራች ወኪሎች ሰርግ እና ምላሽ ሆኗል፡፡ በአንጻሩ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑት እና ኑሯቸውን ለሳዑዲ ሴቶች የሹፍርና አገልግሎት በመስጠት ላይ ለመሰረቱ የውጭ ሐገር ዜጎች አዋጁ መርዶ ሆኖባቸዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለም በመጪው ሰኔ ወር የሚጀመረውን የማሽከርከር ፍቃድ መታገስ ተስኗቸው መኪናዎቻቸውን እያሽከረከሩ ጎዳና ከወጡ የሳዑዲ ሴቶች መካከል አንዷ አደጋ ማድረሳቸው የሰሞኑ ርዕሰ ዜና ነበር፡፡
ስለሺ ሽብሩ
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ