ለአፍሪቃ የፖሊሲ አማራጮች የሚጠቁመው መፅሐፍ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 9 2010ማስታወቂያ
317 ገፆች ያሉት መፅሐፍ Making Africa Work የተሰኘ ርዕስ አለው። ጸሐፊዎቹ ለበርካታ የአፍሪቃ ፕሬዝዳንቶች በአማካሪነት ያገለገሉት ግሬግ ሚልስ፤ በአፍሪቃ ላይ ያተኮሩ መፃህፍት ከዚህ በፊት ለንባብ ያበቁት ጄፍሪ ሔርብስት፣የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ እና የቀድሞብ የብሪታኒያ ጦር ባልደረባ ዲኪ ዴቪስ ናቸው። ፀሀፊዎቹ ያነሷቸው ሐሳቦች እና የጠቆሟቸው የመፍትሔ አስተያየቶች ወቅታዊ የመሆናቸውን ያህል የአፍሪቃ ፖሊሲ አውጪዎች እና አስፈፃሚዎች ይጠቀሙባቸዋል የሚል ተስፋ ተሰንቋል።
ገበያው ንጉሴ
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ