1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለአሳንዥ ጉዳይ የተሰጠው ውሳኔና ስዊድን

ዓርብ፣ ጥር 27 2008

ለንደን በሚገኘው የኢኳዶር ኤምባሲ ጥገኝነት ጠይቆ ከገባ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረዉ የዊኪሊክስ መስራች ጁልያን አሳንጅ በፍርደ ገምድል ሁኔታ እስር ላይ ነዉ ሲል በተመድ የፍትህ ጉዳይ ምሁራን ቡድን ገለፀ ።

https://p.dw.com/p/1HqZ3
Großbritannien Julian Assange auf dem Balkon der ecuadorianischen Botschaft
ምስል Reuters/P. Nicholls

መቀመጫዉን ዤኔቭ ያደረገዉና በተመድ ሥር በፍርደ ገምድል ሁኔታ እስር ላይ ስለሚገኙ ሰዎች ጉዳይ የሚከታተለዉ የምሑራን ቡድን መግለጫ፤ እንደሚያሳየዉ አዉስትራልያዊዉ አሳንጅ፤ ከብሪታንያና ከስዊድን ካሳ ሊከፈለዉ ይገባል። አሳንጅ በብሪታንያ ተይዞ ለስዊድን ተላልፎ እንዳይሰጥ በመፍራት በጎርጎረሳዉያኑ 2012 ዓ,ም ለንደን በሚገኘዉ በኢኳዶር ኤምባሲ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወቃል። የስዊድን መንግሥት አሳንጅን አስገድዶ በመድፈር ወንጀል ክስ እንደቀረበበት ሲያስታወቅ ፤ አሳንጅ የተጣለበትን ክስ ሃሰት ሲል ያጣጥላል። በስዊድን የስቶኮልሙ ወኪላችን ዘገባ ልኮልናል።


ቴዮድሮስ ምህረቱ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ