1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለስደተኞች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጀርመን

ረቡዕ፣ ኅዳር 29 2008

በቅርቡ ደግሞ የኮምፕዩተር ጠበበት ወጣት ሥራ አጥ ስደተኞችን በኮምፕዩተር አሠልጥነው በሥራ ዓለም እንዲሰማሩ በማገዝ ላይ ናቸው ። ከዋና ከተማዋ ከበርሊን የመጣው ይህ ሃሳብ በኮሎኝ ከተማም ተግባራዊ ሆኗል ።

https://p.dw.com/p/1HKrl
Beruf Integrationsberater
ምስል picture-alliance/dpa/F. Kästle

ለስደተኞች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጀርመን



ከቅርብ ወራት ወዲህ ጀርመን ለገቡ በርካታ ስደተኞች ጀርመናውያን ልዩ ልዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ናቸው ። የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስደተኞችን ያስተምራሉ ፣ ሀኪሞችና ነርሶች የነፃ ህክምና አገልግሎት ይሰጣሉ ። ከፊሉ ባዶ ቤቱን ለቆላቸዋል ፣ ጡረታ የወጡ አስተማሪዎችም እውቃታቸውን በፈቃደኝነት እያጋሩ ነው ። እነዚህ ሁሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የሚከናወኑት ያለ መንግሥት እገዛ ነው ። በቅርቡ ደግሞ የኮምፕዩተር ጠበበት ወጣት ሥራ አጥ ስደተኞችን በኮምፕዩተር አሠልጥነው በሥራ ዓለም እንዲሰማሩ በማገዝ ላይ ናቸው ። ከዋና ከተማዋ በርሊን የመጣው ይህ ሃሳብ በኮሎኝ ከተማም ተግባራዊ ሆኗል ። የዛሬው ከኤኮኖሚው ዓለም ትኩረት ነው የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አዘጋጅቶታል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ኂሩት መለሰ