1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሀዘን ያጠላበት ኢሬቻ በሰሜን አሜሪካ፤

ማክሰኞ፣ መስከረም 24 2009

በኢትዮጵያ ቢሾፍቱ ከተማ ሊከበር በተዘጋጀዉ የኢሬቻ በዓል ለሞቱ ወገኖች መንግሥት የተሰማዉን ሀዘን በመግለጽ ብሔራዊ ሀዘን ቀን አዉጇል። ይህን ክስተት ተከትሎ በሰሜን አሜሪካ፤ ካናዳ እና ዩናይትድ ስቴትስ የተከበረዉ የኢሬቻ በዓል ሀዘን አጥሎበት ነዉ የተጠናቀቀዉ።

https://p.dw.com/p/2QpyN
Äthiopien Tote bei Anti-Regierungs-Protesten in Bishoftu
ምስል DW/Y. Gegziabher

Ber. AA (Irecha-Protest) - MP3-Stereo

በዚሁም መሠረት በሀገር ዉስጥ እና በዉጭ የሚገኙ ኤምባሲዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ይዘዉ በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ሠንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ እንዲዉለበለብ መታዘዙን ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል። ብሔራዊ የሀዘን ቀኑ ለሦስት ቀናት የሚዘልቅ ነዉ።  ከሀገር ዉስጥ የሚወጡ የተለያዩ ዘገባዎች ከ50 በላይ ሰዎች ህይወት ከጠፋበት ከትናንቱ ክስተት ማግስት ዛሬም በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ተቃዉሞ መቀጠሉን ያመለክታሉ። ትናንት ማምሻዉን ከአዲስ አበባ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዉ ቢሾፍቱ ከተማ እና በአምቦ በፀጥታ ኃይሎች እና በተቃዉሞ እንቅስቃሴ አድራጊዎች መካከል የተነሳዉ ግጭት ዛሬም መቀጠሉን እማኞችን እና የመንግሥት ባለስልጣናትን የጠቀሱት ዘገባዎች ዘርዝረዋል።

Äthiopien Tote bei Anti-Regierungs-Protesten in Bishoftu
ምስል DW/Y. Gegziabher

በተያያዘ ዜና በየዓመቱ የክረምቱን ማብቃት ተከትሎ የኦሮሞ ብሔር ፈጣሪዉን የሚያመሰግንበት ኢሬቻ በመባል የሚታወቀዉ በዓል ካናዳ እና ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ትናንት ተከብሮ መዋሉ ተሰምቷል። ሀገር ዉስጥ በብዙ ሚሊየን በሚቆጠሩ ሰዎች ደምቆ የሚከበረዉ በዓል በዉጭዉ ዓለምም ባህልና ትዉፊቱን ጠብቆ ለዓመታት ሲከበር ቆይቷል። የዴሞክራሲያዊዉ የገዳ ሥርዓት አንዱ መገለጫ የሆነዉ የኢሬቻ በዓልን ዘንድሮ ያከበሩት በሀዘን መሆኑንም ለዶቼ ቬለ አስተያየታቸዉን የሰጡት ወገኖች ገልጸዋል። 

 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር/መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ