1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሀንጋሪ፣ ስሎቫኪያ እና የአውሮጳ ፍርድ ቤት ብይን

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 2 2009

ሁለቱ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ሀንጋሪ እና ስሎቫኪያ ወደፊት ስደተኞችን መቀበል ይኖርባቸዋል ሲል የአውሮጳ ፍርድ ቤት በየነ። ሁለቱ ሀገራት የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን አባል ሀገራት ስደተኞችን በመካከላቸው በኮታ እንዲከፋፈሉ ያቀረበውን ጥያቄ ለመቀበል እንደማይፈልጉ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/2jXGj
Europäischer Gerichtshof in Luxemburg
ምስል Reuters/F. Lenoir

ሀንጋሪ እና ስሎቫኪያ ወደፊት ስደተኞችን መቀበል ይኖርባቸዋል።

ፍርድ ቤቱ በዚሁ ትናንት ባሳለፈው ብይኑ ሁለቱ የምሥራቅ አውሮጳ ሀገራት የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን አባል ሀገራት ስደተኞችን በመካከላቸው እንዲከፋፈሉ ባቀረበው ጥያቄ አንጻር ቀደም ሲል የመሰረቱትን ክስ ውድቅ አድርጎታል። ሰዎች በብዛት ወደ አውሮጳ በፈለሱበት ድርጊት የተፈጠረውን አጣዳፊ ሁኔታ ኮሚሽኑ በማጉላት፣ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ስደተኞችን በማስተናገዱ ረገድ በግሪክ እና በኢጣልያ ላይ ያረፈውን  ጫና አባል ሀገራት እንዲጋሩ ለማድረግ የተሰጠ ትክክለኛ ብይን ነው በሚል በደስታ ተቀብሎታል። ሀንጋሪ ግን ብይኑን እንደማትቀበል አስታውቃለች።

ገበያው ንጉሤ

አርይም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ