1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Wikileak የተባለው ድረ ገጽ ያወጣው ምሥጢርና የአሜሪካ መንግሥት፣

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 20 2002

ዊኪሊክ» በተባለው ድረ ገጽ፤ ስለአፍጋኒስታኑ ጦርነትና ስለፓኪስታንም ሥውር ሚና የወጣው መረጃ ፣ «የአሜሪካን ደኅነነት ሥጋት ላይ የሚጥል፣

https://p.dw.com/p/OW0K
የ«ዊኪሊክ«ድረ-ገጽ ኀላፊ ጁሊያን አሳንጅ፣ምስል picture alliance/dpa

ኀላፊነት የጎደለው ተግባር ነው» ሲል፣ የኦባማ አስተዳደር ገልጿል። የድረ ገጹ ባለቤት በበኩላቸው፣ መረጃዎቹ፤ ለህዝብ መድረስ እንዳለባቸው ጠቁመው «ለመሠረታዊ የውጭ የፖለቲካ መርኅ ለውጥ መነሻ ሊሆኑ ይችላሉም» ብለዋል። ዊኪሊክ፤ ማንም ሰው፣ ሊያነበውና ተጨማሪ መረጃ ሊያክልበት የሚችል የተጋለጡ ሚስጥሮች ስብስብ ማቅረቢያ ድረ ገጽ እንደማለት ሲሆን፤ ይኸው ድረ-ገጽ ባለፈው እሁድ ይፋ ያደረጋቸው ከ 75 ሺ በላይ ምሥጢራዊ ሰነዶችና መረጃዎች ለዋሽንግተን የራስ ምታት ሆኖባታል። እነዚህ ይፋ የወጡ መረጃዎች፤ በየዕለቱ፤ የአፍጋኒስታትንን የጦር ዐውድ የሚዘረዝሩ ናቸው።

አበበ ፈለቀ

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ