1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ የፊልም ፌስቲቫል ኦጋዱጉ

ረቡዕ፣ የካቲት 22 2009

አፍሪቃዉያን የፊልም አዘጋጆች ሥራቸዉን ለዉድድር የሚያቀርቡበት በቡርኪናፋሶ ዋና ከተማ ዋጋዱጉ ላይ የሚካሄደዉ የፊልም ፌስቲቫል ዛሬ አምስተኛ ቀኑን ይዟል። ለ10 ቀናት በሚዘልቀዉ በምሕጻሩ ፌስፓኮ በመባል በሚታወቀዉ በዚህ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ለአንድ መቶ ሺህ ተመልካቾች ከ100 የሚበልጡ ፊልሞች ለዕይታ እንደሚቀርቡ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/2YTpu
Afrika-Filmabend: Gerreta und Rumeurs du Lac
ምስል Sileshi Siyoumnor / Neon Rouge

Q&A Manti FESPACO - MP3-Stereo

 በዚህ የፊልም ሥራዎች ዉድድር ላይ ለመጨረሻዉ ምርጫ ከቀረቡት 20 ፊልሞች መካከልበአጭር ፊልሞች ዘርፍ የሚሳተፈዉ ባልደረባችን ማንተጋፍቶት ስለሺ ሥራ ግርታ  የተሰኘዉ ፊልምም ተካቷል። ከእሱ ሌላም ፍሬ የተሰኘ ረዥም ፊልሙን ይዞ የቀረበዉ ክንፈ ማሞ በዚሁ ዉድድር በመሳተፍ ላይ ይገኛል። እስካሁን የደረሱበትን ዉጤት ለመገመት ቢከብዳቸዉም ፊልሞቻቸዉ በታዩባቸዉ የተለያዩ አዳራሾች ከተመልካች አበረታች ምላሽ ማግኘታቸዉን ሁለቱም ኢትዮጵያዉያን የፊልም አዘጋጆች ገልጸዉልናል። ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ወደ ኦጋዱጉ ደዉዩ በአጭሩ አነጋግሬያቸዋለሁ። በቅድሚያ ያገኘሁት ባልደረባዬ ማንተጋቶትን ነዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ