1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

CDU/CSU እየመራ ነዉ: SPD -ታሪካዊ ዉድቀት ነዉ

እሑድ፣ መስከረም 17 2002

ዉጤቱ በዚሁ ከፀና CDU/CSU ከ FDP ጋር ተጣማሪ መንግሥት መመሥረት የሚያስችላቸዉ አብላጫ ድምፅ አግኝተዋል።

https://p.dw.com/p/JqAH
CDU/CSU-ደጋፊዎች ፌስታምስል AP

የጀርመን ምርጫ-2002/ የመጀመሪያዉ ዉጤትበዛሬዉ ምርጫ መራሒተ-መንግሥት አንጌላ ሜርክል የሚመሩት የCDU/CSU እትማማች ፓርቲ በከፍተኛ ዉጤት እየመራ ነዉ።እንደ ጀርመን አቆጣጠር እስከ አስራ-ሁለት ሰአት ከሩብ ግድም ድረስ ከመራጮች በተሰባሰበዉ አስተያየት መሠረት CDU/CSU ከተሰጠዉ ድምፅ 33.35 ከመቶዉን በማግኘት የመጀመሪያዉ ሥፍራ ይዟል።እስካሁን በሥልጣን ላይ ያለዉን ተጣማሪ መንግሥት ከCDU/CSU ጋር የመሠረተዉ የሶሻል ዴሞክራቶቹ ፓርቲ SPD 22.7 ከመቶ ድምፅ በማግኘት የሁለተኝነቱን ደረጃ ይዟል።የእስካሁኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየርን ለመራሔ-መንግሥትነት ያጨዉ SPD እንዲሕ አይነት ዝቅተኛ ዉጤት ሲያገኝ በጀርመን ፌደራላዊ ሪፐብሊክ የምርጫ ታሪክ የመጀመሪያዉ ነዉ።የሊብራል ዴሞክራቲክ ፓርቲ FDP 14.6፥ የግራዎቹ ፓርቲ 12.5፥ አረንጓዴዎቹ 10.2 ከመቶ አግኝተዋል።ዉጤቱ በዚሁ ከፀና CDU/CSU ከ FDP ጋር ተጣማሪ መንግሥት መመሥረት የሚያስችላቸዉ አብላጫ ድምፅ አግኝተዋል።

-የምክር ቤት መቀመጫ ድልድልና ተጨማሪ አሐዛዊ ማብራሪያዎችን ለማየት «የጀርመን ምርጫ 2002 ግራፍ (ሰንጠረዡን ይመልከቱ)

ነጋሽ መሐመድ