1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

75 ኛዉ የድል ቀን በድመቀት ተከበረ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 27 2008

ኢትዮጵያ ዉስጥ ዛሬ 75 ኛዉ የድል ቀን በድመቀት ተከበረ። በተለይ በአዲስ አበባ አራት ኪሎ የድል ሐዉልት በሚገኝበት ሥፍራ በድማቅ መከበሩን አዲስ አበባ የሚገኘዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ የላከልን ዘገባ ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/1IioB
Äthiopien 75. Jahrestag der Patrioten in Addis Abeba
ምስል DW/G. Tedla

ሳምንቱን ሙሉ ሲከበር የዘለቀው 75ኛው ዓመት የአልማዝ እዮቤልዩ ድል በአል ዛሬ በደማቅ ሥነ- ስርዓት ተከብሮአል። ኢትዮጵያውያን ወራሪውን የፋሺስት ኢጣሊያ ኃይል ለማባረር ከአራቱም ማዕዘናት ያላቸውን ሁሉ ታጥቀው ሲዘምቱ አንድነታቸው ጠንካራ ነበር። ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ምለአምስት ዓመታት ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት ሙከራ ላይ የነበረዉ የጣሊያን ፋሺስት ሠራዊት ተሸንፎ ንጉሰ ነገስቱ ወደ መንበራቸው ዳግም መመለሳቸዉ ይታወሳል። ባለፉት ቀናቶች ኢትዮጵያ የአርበኞች ማኅበር 75ኛ ዓመት ኢዮቤልዩ ለማክበር ሲዘጋጅ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር የ75ኛዉን የአልማዝ ኢዮቤልዩ ከፋሺስት ጣሊያን ጋር የተካሄደዉን ዉጊያ ጨምሮ ያለፉት የትግል ዘመናት ባልተዛባ ሁኔታ እንዲዘከሩና እና የታሪክ ሠሪዎቹም ገድል ሊታወቅ ይገባል በሚል የቴክኒክ አጋር እንዲሆነዉ ከኢትዮጵያ የደራሲያን ማኅበር ጋር በመተባበር መግለጫ መስጠታቸዉ ይታወሳል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ