74ኛዉ የድል በዓል
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 27 2007ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ከፋሽስት ኢጣሊያ የአምስት ዓመት ወረራ ነፃ የወጣችበት ሰባ-አራተኛ ዓመት የድል በዓል ዛሬ በመላ ሐገሪቱ ተከብሮ ዋለ።በዓሉ በተለይ አዲስ አበባ ዉስጥ በአራት ኪሎዉ የድል ሐዉልት አጠገብ የተከበረዉ ጥንታዊ አርበኞች፤የመንግሥት ባለሥልጣናትና ታዳጊ ወጣቶች በተገኙበት ሥርዓት ነዉ።የዘንድሮዉ በዓል ታዳሚዎች በጦርነቱ ወቅት ከኢትዮጵያዉያን አርበኞች ጎን ተሰልፈዉ የተዋጉትን ለጥቁር አሜሪካዊ ፓይለት ኮሎኔል ጆን ቻርልስ ሮቢንሰንን በልዩ ሥርዓት ዘክረዋቸዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ተጨማሪ ዘገባ አለዉ።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ