1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

30ኛ ዓመቱን የያዘዉ የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስትያን

እሑድ፣ ሰኔ 23 2005
https://p.dw.com/p/18ylx

በጀርመን የመጀመርያዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የተቋቋመበትን ሰላሳኛ ዓመት እንሆ አከበረ።  በጀርመን በኮሎኝ ከተማ የሚገኘዉ የኢትዮጵያዉያን ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን የተቋቋመበትን ሠላሳኛ ዓመት በደማቅ ሲያከብር፤በጀርመንና በአካባቢዋ የሚገኙ ካህናት እና እጅግ በርካታ ምዕመናን እንዲሁም በጀርመን የሚገኙ የተለያዩ የአብያተ ክርስትያናት ተወካዮች በተገኙበት፤ ለሁለት ቀናት ተከብሮአል። የክብረ በዓሉ ታዳሚ ሆነን፤ ምዕመናኑ አነጋግረን፤ በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን ጉዞዉ በጥቂቱ ልናስቃኝ ቅንብር ይዘናል።

አዜብ ታደሰ