29ኛዉ የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ቅድመ ዝግጅት
ረቡዕ፣ ሰኔ 21 2009ማስታወቂያ
እንደተለምዶ ሁሉ ለጉባዔዉ ዝግጅት በቅድምያ በአምባሳደሮች ዉይይት የሚጀምረዉ ሥነ-ስርዓት የፊታችን ሃሙስ እና አርብ የሚንስትሮቹ ስብሰባን በማስከተል በመጭዉ ሳምንት ሰኞና ማክሰኞ የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ተካሂዶ ይጠናቀቃል። በዚህ ጉባዔ የደቡብ ሱዳን ቀዉስ ዋነና የመነጋገርያ አጀንዳ ነዉ ተብሎ ይጠበቃል። አዲስ አበባ የሚገኘዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ከፖለቲካ ተንታኝ ከዶክተር መሐሪ ታደለ ማሩ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጎ ዘገባ ልኮልናል። ዶ/ር መሐሪ ታደለ ጉባዔዉ በተለይ ሰላምና መረጋጋትን በተመለከተ መቋጫ ያጣዉ የደቡብ ሱዳን ዉዝግብ እና ቀዉስ ላይ እንደሚወያይ በመግለፅ ቃለ ምልልሱን ይጀምራሉ።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ