25ኛ ዓመት የነጻነት በዓል
ማክሰኞ፣ ግንቦት 16 2008ማስታወቂያ
በ1985 በተደረገ በሕዝበ ዉሳኔ ከኢትዮጵያ ተነጥላ ነፃ ሀገር የሆነችዉ ኤርትራ ምንም እንኳን በሰብዓዊ መብቶች ይዞታ ትችት ቢሰነዘርባትም ዕለቱን ዛሬ በደመቀ ሁኔታ ማክበሯን የዜና አዉታሮች አመልክተዋል። የአማፅያኑን ኃይል ለድል እንዳበቁ የሚነገርላቸዉ የ70 ዓመቱ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ያኔ ስልጣን ከያዙ ወዲህም በሀገሪቱ ምንም ዓይነት ምርጫ ተደርጎ አያዉቅም። ያኔ አስመራ የነበረዉ ዘጋቢያችን ጎይቶም ቢሆን አሁን ፍራንክፈርት ይገኛል። በስልክ አነጋግረነዋል።
ጎይቶም ቢሆን
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ