1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

16 ኛዉ የICASA ጉባኤ እና ወጣቱ

ዓርብ፣ ኅዳር 29 2004

አዲስ አበባ ላይ ለአራት ቀናት የተሰየመዉ 16 ኛዉ አለማቀፍ የኤድስ እና የአባላዘር በሽታዎች አብይ ጉባዔ በያዝነዉ ሃሙስ ምሽት ተጠናቆአል።

https://p.dw.com/p/S0lk
ምስል DW

ሰባት ሽህ እድምተኞች እንደተካፈሉበት የተገለጸዉ ይህ ጉባኤ ከአለም አገራት የተዉጣጡ ወጣቶችም ተሳትፈዉበታል ልምዶችንም ተለዋዉጠዉበታል። የአራት ቀናቱ ጉባኤ ከመጀመሩ በፊት በርካታ ወጣቶችን ያሳተፈ ዉይይትና የልምድ ልዉዉጥም እንተካሄደ ተገልጾአል። ይህን ጉባኤ ያስተናገደችዉ ኢትዮጽያ እንደ አስተናጋጅነትዋ ወጣቶች በጉባኤዉ እንብዛም እንዳልተሳተፉ ሲነገር በሌላ በኩል ከሌሎች አገሮች ከመጡ ወጣት ተሳታፊዎች ጋር ዉይይት ለማድረግ ለበርካታ ኢትዮጽያዉያን ወጣቶች የመግባብያ ቋንቋ ችግር እንደነበረም ተገልጾአል። በለቱ ዝግጅታችን በአፍሪቃ የወጣቶች ማህበር የምስራቅ አፍሪቃ አገሮች ተወካይ ወጣት ሳባ ባዲ በጉባኤዉ ላይ ተካፋይ ስትሆን በአፍሪቃ ወጣት ሴቶች በባህልና በኢኮነሚ ችግር ለኤድስ ቫይረስ እና ለመሳሰሉ የአባላዘር በሽታዎች ተጠቂ የሆኑበትን ጉዳይ የሚያሳይ ጽሁፍ አቅርባ ነበር። በለቱ ዝግጅታችን ይዘናታል። ከጋና አክራ ጉባኤዉን ለመሳተፍ የመጣዉ ጋናዊ ወጣት ጉባኤዉን አስመልክቶ ስለወጣቶች ተሳትፎ የሚለን ይኖረዋል። ሙሉ ቅንብሩን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ