14 የፖለቲካ ድርጅቶች መሰረዛቸው
ረቡዕ፣ ግንቦት 10 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 14 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ከምዝገባ መሰረዙን አስታወቀ ። የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ፓርቲዎቹ ከተሰረዙባቸው ምክንያቶች ውስጥ ራሳቸው አፅድቀው እንመራበታለን ባሉበት ደንባቸው ላይ ባስቀመጡት የጊዜ ገደብ ጠቅላላ ጉባኤ አለመጥራታቸው ፣ በኦዲተር የተረጋገጠ የሃብት ሰንድ አለማቅረባቸው እና የፅህፈት ቤቶቻቸውንና አድራሻዎች ለቦርዱ አለማሳወቃቸው ይገኙበታል ። እነዚህኑ ፓርቲዎቹ ለረዥም ጊዜ መታገሱን ያሳወቀው ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎቹ የተባሉትን ባለማድረጋቸው ማገዱን አስታውቋል ። ዝርዝሩን የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ