(1)በአርክቲክና በአንታርክቲካ የበረዶ መቅለጥ ያሳዳረው ሥጋት፣ (2)የሰረንጌቲ ባለውለታ፣
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 22 2001ማስታወቂያ
የመፈረካከስ አደጋ እንደተደቀነበት፣ ተነገረ። በሰሜናዊው አንታርክቲካ፣ «የዊልክንስ የበረዶ ንጣፍ በመባል የታወቀው በረዶ የሸፈነው ቦታ፣ባለበት መርጋት አለመቻሉንና መፈርከሱን ያስረዱት፣ በጀርመን የሙዑንስተር ዩኒቨርስቲ የበረዶ ይዞታዎች ተመራማሪ ወ/ሮ አንጌሊካ ሁምበርት ናቸው። ሁምበርት እንዳሉት በአንታርክቲካ ከውቅያኖስ ጋር ፣ ድንበር የሚፈጥር አዲስ የረጋ በረዶ ወሰን እስኪሠት ድርስ፣ አሁን ሰሚናዊው ጫፍ ላይ ያለው፤ ከ 570- 3,370 እስኩየር ኪሎሜትር የሚገመት፣ የበረዶ ጉብታ፣ በሚመጡት ቀናት ተፈርክሶ ውቅያኖስ ላይ መንሳፈፉ አይቀሬ ነው።
ተመራማሪዋ፣ ይህን ያሉት፣ የአውሮፓው የኅዋ ድርጅት ሳቴላይት ያነሳቸውን ፎቶግራፎች ከመረመሩ በኋላ ነው። የ «ዊልክንስ » የበረዶ ንጣፍ 16,000 እስኩየር ኪሎሜትር ያህል ስፋት የነበረው ሲሆን እ ጎ አ፣ በ 1990ኛዎቹ ዓመታት መሸርሸር ጀምሮ አሁን ከደረስንበት ደረጃ ላይ ደርሷል።
ተክሌ የኋላ፣