| ይዘት | DW | 02.03.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ይዘት

ዶቼቬለ የአማርኛ አገልግሎት፥- የበርካታ አድማጮቹን ጥያቄ ከግምት በማስገባት እና በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ በጉዳዩ ላይ የተደረገውን ጥናት በመመርኮዝ የስርጭት ጊዜ ለውጥ ያደርጋል ። በዚሁ መሰረት እስካሁን ከቀኑ 11 :00 እስከ 12 :00 ሠዓት በአጭር ሞገድ ይተላለፍ የነበረውን ዝግጅቱን ከመጋቢት 18 ቀን 2003 ጀምሮ ከ ምሽቱ 1:00 እስከ ምሽቱ 2 :00 ሠዓት ማሰራጨት ይጀምራል ። ከ1957 አንስቶ በራድዮ የሚያሰራጨው ዶቼቬለ በዘመኑ ቴክኖሎጂም ከአድማጮቹ ይደርሳል ። ማንኛውም አድማጭ ዝግጅቶቹን በድረ ገፅ፣ በፖድካስት፣ በፌስ ቡክ እና በትዊተርም መከታተል፣ መሳተፍም ይችላል ። ስርጭታችን በሳተላይት በናይል ሳት 7 ዲግሪ West ፣ Frequency 11,900 MHz እና Symbolrate 27,50 ላይም ይደመጣል ። የቀጥታ ስርጭታችን ካመለጣችሁ www.dw-world.de/amharic ድረ ገፃችን ላይ የየቀኑን ስርጭት ለአንድ ሳምንት ማዳመጥ ይቻላል ። በ http://www.facebook.com/dw.amharic እና http://twitter.com/dw amharic ስለ ወቅታዊ ጉዳዮች በሚቀርቡት ዝግጅቶች ላይ በፌስ ቡክ እና በትዊተር አስተያየቶችን መለዋወጥም ትችላላችሁ ። ዓለምን ለመረዳት-ዶቼቬለን ያዳምጡ !