| ኢትዮጵያ | DW | 01.06.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የክብረ አረጋዊያን ምግባረ ሰናይ ድርጅት እና እንቅስቃሴው የአፍሪቃ ልማት ባንክ እኢአ 2011 ባወጣው አንድ ጥናት ከአፍሪቃ ህዝብ 36 ሚሊዮኑ አረጋውያንን መሆናቸውን አስፍሯል። እንደ HELP AGE INTERNATIONAL የተባለው ድርጅት የ 2011 ጥናት ደግሞ ከኢትዮጵያ ህዝብ4,1 ከመቶው እድሚያቸው 60 እና ከዛ በላይ መሆናቸውን አትቷል።

አብዛኛው አረጋውያን የራሳቸው ገቢ የላቸውም፣የጤና እና የምግብ ችግሮችም ይገጥማቸዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ በመንግስት የተቋቋሙ የአረጋዊያን መጠለያዎች በበቂ ሁኔታ ባይኖሩም አንዳንድ ችግሩን ለመፍታት የሚሞክሩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች አልጠፉም። ኑሯቸውን ፈረንሳይ -ፓሪስ ባደረጉ አንዲት ኢትዮጵያዊት ኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመው « ክብረ ለአረጋዊያን ምግባረ ሰናይ ድርጅትም» ተስፋ ለቆረጡና ረዳት ላጡ በርካታ አረጋውያን እንደደረሰ ይገልፃል። የፓሪሷ ዘጋቢያችን ሐይማኖት ጥሩነህ የዚህን ድርጅት መስራች አነጋግራ የላከችልን ዘገባ አለ።

ሐይማኖት ጥሩነህ

ልደት አበበ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic