ፍጥረተ ዓለምና የስበት ኃይል ሞገዶች | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 26.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

ፍጥረተ ዓለምና የስበት ኃይል ሞገዶች

ለፍጥረተ ዓለም(ዩኒቨርስ)መከሠት ፤ መገኘት ፤ መዘርጋት-- መንስዔ ነው ተብሎ የሚጠቀሰው «ታላቁ ፍንዳታ» (BIG BANG) ከ 14 ቢሊዮን ዓመት ገደማ በፊት ማጋጠሙን የሚጠቁም መረጃ በምርምር አግኝተናል ሲል አንድ የጠፈር ሳይንቲስቶች በድን ከወዲያኛው ሳምንት መግለጹ የሚታወስ ነው።

ለ«ኮስሞስ» (ፍጥረተ ዓለም) በእጅጉ መዘርጋት፤ ግሽበትም ተብሏል --ፍንጭ ሰጪ ነው የተባለው ግኝት ፣ የስበት ኃይል ሞገዶች (Waves of Gravity) የሚሰኘውን ነው የሚመለከተው።
በደቡብ የምድር ዋልታ በተተከለና በፍጥረተ ዓለም ስለመሰረታዊው፦ ጥንታዊው ብርሃን በመመራመር በሚለካው የሩቁን እጅግ አጉልቶ በሚያሳየው መሣሪያ (ቴሌስኮፕ) ርዳታ አማካኝነትም ነው ስለ መጀመሪያዎቹ የስበት ኃይል ሞገዶች ለማወቅ ተችሏል የተባለው። በአንድ ቡድን የተገኘውን ይህን የምርምር ውጤት ሌሎች ጠበብትም ከተስማሙበት፤ ተመራማሪዎቹን ለኖቤል ሽልማት እንዲታጩ ሊያደርጋቸው እንደሚችልም የገመቱ አልታጡም።
የስበት ኃይል ሞገዶች አሁን በምርምር የታወቁበት ሁኔታ የ«ታላቁን ፍንዳታ » ነባቤ ቃል የሚያጠናክር ነው እንደ ተመራማሪዎቹ አባባል፣ አሁን ከተሠለፉበት ቀጥተኛ ግንኙነት ባይኖረውም፣ ከዩናይትድ ስቴትሱ የኅዋ ምርምርና የበረራ ጉዳዮች አስተዳደር መ/ቤት ጋር ተባብሮ በሚሠራው ቦስተን ኮሌጅ ፣ የኅዋ (ጠፈር) ሳይንስ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑትን ኢትዮጵያዊ ምሁር ዶ/ር እንዳወቀ ይዘንጋውን ይኸኛው የአስትሮፊዚክስ ዘርፍ ፣ ካሁኑ የዕለት- ተለት ተግባራቸው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ባይኖረውም፤ ካጠቃላይ ዕውቀት በመነሣት ያብራሩልን ዘንድ ጠይቄአቸው ነበር---


ያለፈው ምዕተ ዓመት ታላቁ ሳይንቲስት አልበርት አይንሽታይን፤ ከዚህ ጨረር በስተጀርባ የስበት ኃይል ሞገድ አለ ሲል፤ የስበት ኃይልን በሚመለከተው አጠቃላይ የ«ሪላቲቪቲ»ነባቤ -ቃልም ሆነ ንድፈ-ሐሳብ ገልጾ እንደነበረ የሚታወስ ነው። በደቡብ የምድር ዋልታ በተተከለ ቴሌስኮፕ የተካሄደው መርምር ይህን ምናልባት የሚያረጋግጥ ሊሆን ይችላል። የአልበርት አይንሽታይን ፅንሰ ሐሳብ ጭብጥ ምን ይሆን?!
ጠበብቱ በቴሌስኮፕ ርዳታ ያስተዋሉት ኢምንት ሞገዳዊ ጨረሮች(Micro Wave Radiation) ወደተለያዬ አቅጣጫ ሲጓዙ፤ ሲዘዋወሩ ነው። ኤሌክትሮ ማግኔቲክ ሞገዶች፤ የብርሃንና የስበት ኃይል ሞገዶች፤ ይህ ዓይነት ሁኔታ ይንጸባርቅባቸዋል። የዚህን መለስ-ቀለስ የሚል እንቅሥቃሤ ልዩነት የስበት ኃይል ሞገድ አለ፣የለም ያን በመከታተል በግልጽ ለይተው ማየት ችለዋል። አንድ ጨረር ወዲያና ወዲህ ሲል ወደ ቀኝ ወይ ወደ ግራ የሙቀት መጠን ልዩነት ይኖረዋል። በጣም ኢምንት የሆነ ልዩነት! የዚህን የሙቀት መጠን ልዩነት ለክተው ፣ አጠቃላዩ ስዕል የሰጣቸው፤ የስበት ኃይሉ ሁኔታ ወዲያው ግልጽ ሆኖ ነው የታያቸው። ይህን ካገኙ በኋላ ጠበብቱ ምን ነበረ ያሉት!?
የስበት ኃይል ሞገዶች(ዌቭስ ኦፍ ግራቪቲ) ያሉትን --የሥነ ፈለክ ሊቃውንት ወይም የጠፈር ሳይንቲስቶች፤ በምድራችን ደቡብ ዋልታ ላይ በተካሄደ ክትትል ነው፤ ከዚህ ውጤት ላይ የደረሱት በዚያ የምድራችን ከፊል ኅዋ ቀረብም ጥርትም ብሎ ይታያል የሚባለው በምን ምክንያት ይሆን?ዶ/ር እንዳወቀ ይዘንጋው---

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic